ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 18:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ሹም ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆቹ ደግሞ ከንጉሡ ቀጥሎ የበላይ ሹማምት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮዳሄ ልጅ በናያ የዳዊት ክብር ዘብ አዛዥ ነበር፤ የንጉሥ ዳዊት ወንዶች ልጆች በአባታቸው መንግሥት ከፍተኛ ማዕርግ ነበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ። |
ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር።
ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤
አቢሳና የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያንም፥ ፈሊታውያንም፥ ኀያላኑም ሁሉ ወጥተው ተከተሉት፤ ከኢየሩሳሌምም ወጥተው የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄን አሳደዱት።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፤ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን ወሰዱት።
ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄንም ልጅ በናያስን፥ ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፤ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።
የእግዚአብሔርንም ቤት በየአደባባዩና በየመጋረጃው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞአቸው ነበር።
በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።
እኛም በከሊታውያን አዜብ፥ በይሁዳም በኩል፥ በካሌብም አዜብ ላይ ዘመትን፥ ሴቄላቅንም በእሳት አቃጠልናት” አለው።