1 ዜና መዋዕል 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርህያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊት አለቃ ነበረ፤ የአሔሉድም ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊቱ አዛዥ ነበረ፤ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ የቤተ መዛግብቱ ኀላፊ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽሩያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊቱ አለቃ ነበረ፤ የአሒሉድም ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአቢሳ ወንድም ኢዮአብ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ የቤተ መዛግብት ኀላፊ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽሩያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊት አለቃ ነበረ፤ የአሒሉድም ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበረ። |
ዳዊትም ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኰንን ይሆናል አለ። የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣና ወጋቸው፥ አለቃም ሆነ።