1 ዜና መዋዕል 17:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህ ነገር ሁሉ እንደዚህም ራእይ ሁሉ ነቢዩ ናታን ለዳዊት ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናታንም የዚህን ራእይ ቃል በሙሉ ለዳዊት ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንን ቃል ሁሉ ይህንንም ራእይ ሁሉ ናታን ለዳዊት ነገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ናታን እግዚአብሔር የገለጠለትን ሁሉ ለዳዊት ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህ ነገር ሁሉ እንደዚህም ራእይ ሁሉ ናታን ለዳዊት ነገረው። |
ንጉሡም ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ለዘለዓም የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?
የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር።