1 ዜና መዋዕል 16:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤ በአሕዛብ መካከል፥ “እግዚአብሔር ነገሠ” በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል፤ “እግዚአብሔር ነገሠ!” ይበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል፦ “ጌታ ነግሷል” ይበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰማይና ምድር ደስ ይበላቸው! ሕዝቦች ሁሉ “እግዚአብሔር ንጉሥ ነው” ይበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል “እግዚአብሔር ነገሠ፤” በሉ። |
እግዚአብሔርን የምትወድዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የጻድቃኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።
አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና ቸል አይለንም፤ እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችን ነው። እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ያድነናል።
እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ምሕረትን አድርጎአልና ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና የምድር መሠረቶች መለከትን ይንፉ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በውስጣቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት ደስታ ይሆናል።”
መልአኩም እንዲህ አላቸው፥ “እነሆ፥ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ።
እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።