1 ዜና መዋዕል 16:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴውም ብዙ ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ታላቅ፥ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋልና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ የተፈራ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል፤ ከአማልክት ሁሉ ይበልጥ ሊፈራ ይገባዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነው። |
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።