1 ዜና መዋዕል 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ግፍ እንዲያደርግባቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን ማንም እንዲጨቊናቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “የቀባኋቸውን አትዳስሱ፤ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ፤” ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ። |
በዚያች ሌሊትም አቤሜሌክ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር በሕልም ወደ እርሱ መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርስዋ ባለ ባል ናትና።”
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
አሁንም በአንተ ላይ ክፉ ማድረግ በቻልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአባትህ አምላክ ትናንት፦ በያዕቆብ ላይ ክፉ እንዳታደርግ ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ።
የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሀት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መዋረዴንና የእጆችን ድካም አየ፤ ትናንትም ገሠጸህ።”