ዳዊትም በዜማ ዕቃ፥ በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን “ወንድሞቻችሁን ሹሙ” ብሎ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።
1 ዜና መዋዕል 15:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዋውያኑም አለቃ ኮነንያስ በዜማ ላይ ተሾሞ ነበር። ብልሃተኛ ነበረና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዝማሬው ኀላፊ ሌዋዊው አለቃ ክናንያ ነበረ፤ ይህን ኀላፊነት የወሰደው በዝማሬ የተካነ ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዋውያኑም አለቃ ክናንያ ዜማን አዋቂ ስለ ነበር ዜማውን እንዲመራ ተሾሞ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከናንያ የሙዚቃ ችሎታ ስለ ነበረው ለሌዋውያኑ መዘምራን መሪ ሆኖ ተመረጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዋውያኑም አለቃ ክናንያ በዜማ ላይ ተሾሞ ነበር። ብልሃተኛ ነበረና ዜማ ያስተምራቸው ነበር። |
ዳዊትም በዜማ ዕቃ፥ በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን “ወንድሞቻችሁን ሹሙ” ብሎ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።
ዳዊትም፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ሌዋውያንም ሁሉ፥ መዘምራኑም፥ የመዘምራኑም አለቃ ኮኖንያስ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብሰው ነበር፤ ዳዊትም የከበረ ልብስ ለብሶ ነበረ።