ለንጉሡ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራን ቤትና የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት። ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣት።
1 ዜና መዋዕል 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጽሐፍም እንደ ተጻፈ ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል እንደ አዘዛቸው የሌዋውያን ልጆች የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎቹ ተሸከሙ። መባእና ቍርባንም ከእነርሱ ጋር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው፣ ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎች አድርገው ተሸከሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንዳዘዘው እንደ ጌታ ቃል የሌዋውያን ልጆች የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎቹ ተሸከሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሌዋውያን ታቦቱን በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎች ተሸክመው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንዳዘዘው እንደ እግዚአብሔር ቃል የሌዋውያን ልጆች የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎቹ ተሸከሙ። |
ለንጉሡ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራን ቤትና የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት። ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣት።
ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ ክፍሎች ነበሩ። በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር።
መሎጊያዎቹም ረጃጅሞች ነበሩ፤ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ከመቅደሱ ውስጥ ጫፎቻቸው ይታዩ ነበር፤ በውጭ ግን አይታዩም ነበር፤
እግዚአብሔርም በዖዛ ላይ ተቈጣ። እጁንም ወደ እግዚአብሔር ታቦት ስለ ዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።
መሎጊያዎቹም ረጃጅሞች ነበሩና በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ከመቅደሱ ውስጥ ጫፎቻቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጭ አይታዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።
ሙሴም ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፤ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አደረገ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው።
አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይገባሉ። እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በምስክሩ ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።