ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።
1 ዜና መዋዕል 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “አትውጣ፥ በኋላቸውም አትከተላቸው፤ ነገር ግን ከኋላቸው ዙረህ ቅረባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት “ዙሪያውን ከብበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ ከኋላቸው በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ “ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “ከኋላ በኩል ዞረህ በሾላ ዛፎች አጠገብ በመሆን አደጋ ጣልባቸው እንጂ በዚህ በኩል ሽቅብ ወጥተህ በመሰለፍ አደጋ አትጣልባቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ። |
ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።
ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው።
በሾላውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ሊመታ እግዚአብሔር በፊትህ ይወጣልና በዚያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ” አለው።