ለሰልፍ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች የነበሩ የስምዖን ልጆች ሰባት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ።
ከስምዖን ነገድ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰባት ሺሕ አንድ መቶ።
ለውግያ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች የነበሩ የስምዖን ልጆች ሰባት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ።
ለሰልፍ ጽኑዓን፥ ኀያላን ሰዎች የነበሩ የስምዖን ልጆች ሰባት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ።
የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤
የልያ ልጆች፤ የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤
ጋሻና ጦር ተሸክመው ለሰልፍ የተዘጋጁ የይሁዳ ልጆች ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ነበሩ።
የሌዊ ልጆች አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
በቀባቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የአሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሜካ ልጅ ማታንያስ፤ የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰማያ ልጅ አብድያ፤
በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ።