1 ዜና መዋዕል 1:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የቴማን ሀገር ሰው አሶም ነገሠ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮባብም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዩባብ በሞተ ጊዜ የቴማን አገር ሰው ሑሻም ነገሠ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ። |
ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ።