1 ዜና መዋዕል 1:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖሕ፥ አቢዳን፥ ኤልዳን። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድያም ልጆች፦ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚድያምም ዔፋ፥ ዔፌር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ተብለው የሚጠሩትን አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ። |
የአብርሃም ዕቅብት ኬጡራ የወለደችለት ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳም፥ ምድያን፥ ዮሳብቅ፥ ስዌሕ፥ የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ዳዳን።
የግመሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የምድያምና የኤፋ ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወርቅንና ዕጣንን ይዘው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ማዳን ያበሥራሉ።