ሶፎንያስ 1:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም ቀድሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ! የጌታ ቀን ቀርቧልና፤ ጌታ መሥዋዕትን አዘጋጅቷል የጠራቸውንም ቀድሶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ስለ ቀረበ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመሥዋዕት እንደሚታረድ እንስሳ አሳልፎ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፤ ይሁዳን የሚበዘብዙ ጠላቶችንም ለይቶ አዘጋጅቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ። |
የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ ሥብ ጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣ በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቷልና።
እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።
ያ ቀን ግን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን። ሰይፍ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ ጥማቱም እስኪረካ ድረስ ደም ይጠጣል። በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና።
እናንተ በምድሪቱ የምትኖሩ ሆይ፤ የጥፋት ፍርድ መጥቶባችኋል፤ ጊዜው ደርሷል፤ በተራሮች ላይ እልልታ ሳይሆን ሽብር የሚሰማበት ቀን ቀርቧል።
በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?
በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋራ የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።
ጌታ እግዚአብሔር፣ “በዚያ ቀን የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ወደ ዋይታ ይለወጣል፤ እጅግ ብዙ የሆነ የሰው ሬሳ ወድቆ ይገኛል፤ ዝምታም ይሰፍናል” ይላል።
“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤ በእግዚአብሔር ቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤ በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤
“እነሆ፤ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ ይሆናሉ፤ ያ የሚመጣው ቀንም ያቃጥላቸዋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አያስቀርላቸውም።
“እንደ ገናም ሌሎች ባሮች ልኮ፣ ‘የተጋበዙትን፣ እነሆ፣ በሬዎችንና የሠቡ ከብቶቼን ዐርጄ ድግሱን አዘጋጅቻለሁ፤ ሁሉም ነገር ዝግጁ ስለ ሆነ፣ ወደ ሰርጉ ኑ በሏቸው’ አለ።
ሳሙኤልም፣ “አዎን፤ ለሰላም ነው፤ የመጣሁትም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ላቀርብ ነው፤ እናንተም ራሳችሁን ቀድሳችሁ ከእኔ ጋራ ወደ መሥዋዕቱ ኑ” ሲል መለሰላቸው። ከዚያም እሴይንና ልጆቹን ቀደሳቸው፤ ወደ መሥዋዕቱም እንዲመጡ ጠራቸው።
ሳኦልም፣ “ዳዊት በሥርዐቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፣ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም።