ዘካርያስ 2:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋት ምን ያህል እንደ ሆነ ለመለካት መሄዴ ነው፤” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፦ “እነዚህ ይሁዳን፥ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ ቀንዶች ናቸው” ብሎ መለሰልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅሁት፤ እርሱም “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋት ምን ያኽል እንደ ሆነ ለመለካት መሄዴ ነው” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፦ አንተ ወዴት ትሄዳለህ? አልሁ። እርሱም፦ የኢየሩሳሌምን ወርድና ርዝመት ስንት መሆኑን ሰፍሬ አይ ዘንድ እሄዳለሁ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ አንተ ወዴት ትሄዳለህ? አልሁ። እርሱም፦ የኢየሩሳሌምን ወርድና ርዝመት ስንት መሆኑን ሰፍሬ አይ ዘንድ እሄዳለሁ አለኝ። |
“ ‘ከተቀደሰው ስፍራ ጋራ የተያያዘ ወርዱ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ የሆነ ቦታ ለከተማዪቱ ርስት አድርገህ ስጥ፤ ይህም ለመላው የእስራኤል ቤት ይሆናል።
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በምሕረት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ በዚያም ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከዚያም ሸንበቆ የመሰለ መለኪያ በትር ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ፤ “ሄደህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና መሠዊያውን ለካ፤ በዚያም የሚያመልኩትን ቍጠር።