ለገባዖናውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ገድለው በኰረብታው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፤ የተገደሉትም በመከሩ ወራት የመጀመሪያ ቀኖች፣ የገብስ ዐጨዳ በተጀመረበት ዕለት ነበር።
ሩት 1:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኑኃሚን ከምራቷ ከሞዓባዊቷ ሩት ጋራ በመሆን ከሞዓብ ተመለሰች፤ ቤተ ልሔም የደረሱትም የገብስ አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሪያ ላይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ናዖሚ፥ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር፥ ከሞዓብ አገር ተመለሰች። የገብስም መከር መሰብሰቢያ ጅማሬ ላይ ቤተልሔም መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ናዖሚ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር ከሞአብ አገር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር፤ እነርሱ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ የገብስ መከር የሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑኃሚንም ከእርስዋም ጋር ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ሞዓባዊቱ ምራትዋ ሩት ተመለሱ። የገብስም መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑኃሚንም ከእርስዋም ጋር ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ሞዓባዊቱ ምራትዋ ሩት ተመለሱ። የገብስም መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ። |
ለገባዖናውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ገድለው በኰረብታው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፤ የተገደሉትም በመከሩ ወራት የመጀመሪያ ቀኖች፣ የገብስ ዐጨዳ በተጀመረበት ዕለት ነበር።
“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ ከሰበሰባችሁት እህል የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ አቅርቡ፤