ራእይ 7:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ እነርሱም ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መቶ አርባ አራት ሺሕ ነበሩ፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታተሙትንም ሰዎች ቊጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ የታተሙት ሰዎች ቊጥር መቶ አርባ አራት ሺህ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። |
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምድሪቱን ርስት አድርገህ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ የምታከፋፍሉባቸው ወሰኖች እነዚህ ናቸው፤ ዮሴፍ ሁለት ዕጣ ይኑረው።
የከተማዪቱ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይጠራሉ፤ በሰሜን በኩል ያሉት ሦስቱ በሮች የሮቤል ነገድ በር፣ የይሁዳ ነገድ በርና የሌዊ ነገድ በር ይሆናሉ።
የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤ በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤ የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፏልና።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ በሚመጣው አዲስ ዓለም የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም የተከተላችሁኝ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ፣ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ ትፈርዳላችሁ።
ይኸውም በመንግሥቴ ከማእዴ እንድትበሉና እንድትጠጡ፣ ደግሞም በዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ እንድትፈርዱ ነው።”
ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ከልብ እያገለገሉ፣ ሲፈጸም ለማየት የሚተጉለትም ተስፋ ይኸው ነው። ንጉሥ ሆይ፤ አይሁድም የሚከስሱኝ ስለዚሁ ተስፋ ነው።
ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ ነበር፤ ከርሱም ጋራ የርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራቱ ሺሕ ሰዎች ነበሩ።
እነርሱም በዙፋኑ ፊት፣ በአራቱ ሕያዋን ፍጡራንና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ መዝሙር ዘመሩ። ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺሕ ሰዎች በቀር መዝሙሩን ማንም ሊማረው አልቻለም።