መዝሙር 98:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አዳኝነቱ እንዲታወቅ አደረገ፤ ጽድቁንም ለአሕዛብ ገለጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ። |
እርሱም፣ “ባሪያዬ መሆንህ፣ የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣ የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።
በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሧል!” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።
ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፣ ከእምነትም በሆነ ጽድቅ በርሱ ዘንድ እንድገኝ ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በኩል እንደ ተቀበልነው ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤