La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 94:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለእኔ ግን እግዚአብሔር ምሽግ፣ አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ መጠጊያ ሆነኝ፥ አምላኬ የመጠለያዬ ዓለት ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለእኔ ግን እግዚአብሔር መከታዬ ነው፤ አምላኬ መጠጊያዬ ነው።

Ver Capítulo



መዝሙር 94:22
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤ እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።


ብርታቴ ሆይ፤ አንተን እጠብቃለሁ፤ አምላክ ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህና።


ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።


ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።


ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ


እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።


ሕዝቦችን በተግሣጽ ወደ መንገድ የሚመልስ፣ ዕውቀትንስ ለሰው ልጆች የሚያስተምር አይቀጣምን?


ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም።