መዝሙር 91:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፥ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንበሳንና እባብን ትረግጣለህ፤ በአስፈሪው አንበሳና በመርዛሙ እባብ ላይ ትራመዳለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተተከሉ ናቸው፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ። |
በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣ የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንን በብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤ የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል።
ንጉሥ ሆይ፤ በፊቱ ቅን ሆኜ ስለ ተገኘሁ፣ በአንተም ፊት በደል ስላልተገኘብኝ፣ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጐዱኝም።”
ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙላት እንዲሰበክና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳም መንጋጋ አዳነኝ።
ታላቁ ዘንዶ፣ የጥንቱ እባብ ተጣለ፤ እርሱም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው፣ ዓለምን ሁሉ የሚያስተው ነው፤ እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከርሱ ጋራ ተጣሉ።
ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም፣ “ሂድ፤ እግዚአብሔር ካንተ ጋራ ይሁን” አለው።