ከኤዶታም ወንዶች ልጆች፤ ጎዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።
መዝሙር 77:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ይሰማኝ ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ አሁንም ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፥ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ። |
ከኤዶታም ወንዶች ልጆች፤ ጎዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጸናጽል፣ በመሰንቆና በበገና ድምፅ ለሚቀርበው የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሡ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ።