መዝሙር 68:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይልህን እዘዝ፤ አምላክ ሆይ ቀድሞ እንዳደረግህልን አሁንም ብርታትህን አሳየን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጣቱ ብንያም በጉልበቱ በዚያ አለ፥ ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች፥ የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ኀይልህን ግለጥ፤ ከዚህ በፊት እኛን ያዳንክበትን ብርታትህን አሳይ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥ ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ። |
ይህን እያሰብን አምላካችን ለጥሪው የበቃችሁ አድርጎ እንዲቈጥራችሁ፣ በጎ ለማድረግ ያላችሁን ምኞትና ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን ሁሉ በኀይሉ እንዲፈጽምላችሁ ዘወትር ስለ እናንተ እንጸልያለን።
ሳኦልም፣ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ጐሣዬስ ከብንያም ነገድ ጐሣዎች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለ ምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።