መዝሙር 65:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድረ በዳ መስኮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መስኮች የብዙ በጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤ ሸለቆዎች በሰብል ይሸፈናሉ፤ ሁሉም ደስ ብሎአቸው፥ በእልልታ ይዘምራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ |
በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ። ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።
በምድርም ለዘራኸው ዘር ዝናብን ይሰጥሃል፤ ከመሬትም የሚገኘው ፍሬ ምርጥና የተትረፈረፈ ይሆናል። በዚያ ቀን ከብቶችህ በትልቅ ሜዳ ላይ ይሰማራሉ።
እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
ሰማያት ሆይ፤ እግዚአብሔር ይህን አድርጓልና ዘምሩ፤ የምድር ጥልቆች ሆይ፤ በደስታ ጩኹ። እናንተ ተራሮች፣ እናንተ ደኖችና ዛፎቻችሁ ሁሉ እልል በሉ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቷል፣ በእስራኤልም ክብሩን ገልጧልና።
ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤ ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ! እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤ ለተቸገሩትም ይራራልና።
ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም።
የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤ መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ ዛፎቹ ፍሬአቸውን አፍርተዋል፤ የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል።
ይሁን እንጂ ዝናብን ከሰማይ እንዲሁም ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠቱ፣ ደግሞም ልባችሁን በመብልና በደስታ በማርካቱ መልካምን በማድረግ ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”