መዝሙር 62:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፥ ጠንካራ ዓለቴና መጠለያዬ እግዚአብሔር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች ሆይ! ዘወትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ መጠጊያችን ስለ ሆነ የልባችሁን ሐሳብ ሁሉ ለእርሱ አቅርቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ። |
ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣ እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣ በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣ በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣ እንዴት ከሕዝቡ ጋራ እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።
የሌሊቱ ሰዓት ሲጀምር፣ ተነሺ በሌሊት ጩኺ፤ በጌታ ፊት፣ ልብሽን እንደ ውሃ አፍስሺ፤ በየመንገዱ ዳር ላይ፣ በራብ ስለ ወደቁት፣ ስለ ልጆችሽ ሕይወት፣ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።
ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፤ “ጌታዬ ሆይ፤ ሰክሬ አይደለም፤ እኔ ልቧ ክፉኛ የታወከባት ሴት ነኝ፤ ልቤን በእግዚአብሔር ፊት አፈሰስሁ እንጂ፣ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም።