ባለጠግነትና ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዥ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም ብርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኀይል በእጅህ ነው።
መዝሙር 62:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ ምሕረትም የአንተ ነው፤ አንተ ለእያንዳንዱ፣ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፥ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ሆይ! ለሁሉም እንደየሥራው ስለምትከፍል ዘለዓለማዊ ፍቅር ያንተ ነው። |
ባለጠግነትና ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዥ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም ብርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኀይል በእጅህ ነው።
አንተም፣ “ስለዚህ ነገር ምንም አላውቅም” ብትል፣ ልብን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ሕይወትህን የሚጠብቃት እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን አይከፍለውምን?
ዕቅድህ ታላቅ፣ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ዐይኖችህ የሰው ልጆችን መንገዶች ሁሉ ያያሉ፤ ለእያንዳንዱም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ።
“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
ይሁን እንጂ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ‘የጌታ መንገድ ቀና አይደለችም’ ትላላችሁ፤ ነገር ግን በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።”
ንጉሡ ያለቅሳል፤ መስፍኑ ተስፋ መቍረጥን ይከናነባል፤ የምድሪቱም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች። የእጃቸውን እከፍላቸዋለሁ፤ ራሳቸው ባወጡት መስፈርት መሠረት እፈርድባቸዋለሁ። “ ‘በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት። ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው።
የርስቱን ትሩፍ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።
ለሰው ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በዚህ ምድር በእንግድነት ስትኖሩ በፍርሀት ኑሩ።