መዝሙር 59:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቍጣ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም አስወግዳቸው፤ በዚህም እግዚአብሔር የያዕቆብ ገዥ መሆኑ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይታወቃል። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ አፋቸው ኃጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥ መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ፥ በትዕቢታቸው ይጠመዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቊጣህ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም ደምስሳቸው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያስተዳድርና ግዛቱም በምድር ሁሉ እንደ ተንሰራፋ፥ ሰው ሁሉ ያውቃል። |
“ ‘ቅዱሱ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል ዘንድ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅዱስ ስሜ እንዲናቅ፣ እንዲቃለል አልፈልግም፤ አሕዛብም እኔ እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ከሕዝብ ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ዱር አራዊትም ጋራ ትኖራለህ። እንደ ከብት ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠልም ትረሰርሳለህ፤ ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።
የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ስለ ነደደ፣ በፊቱ ክፉ ነገር ያደረገው ያ ትውልድ በሙሉ እስኪያልቅ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው።