መዝሙር 58:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንበሶቹን መንጋጋ አወላልቅ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! የእነዚህን እንደ አንበሳ አስፈሪ የሆኑ ሰዎች ጥርስ ስበር፤ መንጋጋቸውንም አውልቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል የሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበት፣ ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣ በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።
“እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣ የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ይነድፏችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር።
እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።
በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣ የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣ በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣ እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣ የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።