ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለው፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፣ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጕዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ብሎ አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለ ሆነ፣ አንድ ሺሕ ሰቅል ጥሬ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፣ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም።
መዝሙር 55:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባልንጀራዬ የምለው ሰው እጁን በወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይለወጡምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና ከጥንት ጀምሮ የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቁላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጓደኛዬ ወዳጆቹን አጠቃቸው፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ። |
ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለው፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፣ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጕዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ብሎ አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለ ሆነ፣ አንድ ሺሕ ሰቅል ጥሬ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፣ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም።
የይሁዳም ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ በዚያም ዳዊትን ቀብተው በይሁዳ ቤት ላይ አነገሡት። ሳኦልን የቀበሩት የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች መሆናቸውን ለዳዊት በነገሩት ጊዜ፣
ስለዚህ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
ይህንም ልማዳቸውን እስከ ዛሬ ድረስ አልተዉትም፤ እግዚአብሔርን በአግባቡ አያመልኩም፤ እንዲሁም እስራኤል ብሎ ለጠራው ለያዕቆብ ዘሮች የሰጣቸውን ሥርዐቶችና ደንቦች፣ ሕጎችና ትእዛዞችን አይከተሉም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።
ከዚያም ንጉሡ በአጠገቡ የቆሙትን ዘቦች፣ “እነዚህም የእግዚአብሔር ካህናት ከዳዊት ጋራ ስላበሩ፣ ዳዊት መኰብለሉንም እያወቁ ስላልነገሩኝ ዙሩና ግደሏቸው” ሲል አዘዛቸው። የንጉሡ ሹማምት ግን እጃቸውን አንሥተው የእግዚአብሔርን ካህናት ለመምታት ፈቃደኞች አልሆኑም።
በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደ ጣለህ እነሆ፤ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፣ ‘እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።