መዝሙር 55:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካሄዳቸውን አልቀየሩምና፣ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና፣ ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ ያለ አምላክ፣ ሴላ ሰምቶ ያዋርዳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ ብዙ ነበሩና ከተቃጣብኝ ጦርነት ነፍሴን በሰላም ያድናታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ስለማይለወጡና አምላክን ስለማይፈሩ ለዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ያለው አምላክ የእኔን ጸሎት ሰምቶ ያዋርዳቸዋል። |
“ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም።
“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።”
በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ተንደላቅቀው የሚኖሩትን፣ በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣ ‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።