መዝሙር 138:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤ ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፥ ነፍሴን በኃይልህ አጸናሃት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠራሁህ ጊዜ ሰማኸኝ፤ በብርታትህም አበረታኸኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍለጋዬንና መንገዴን አንተ ትመረምራለህ፤ መንገዶቼን ሁሉ አስቀድመህ ዐወቅህ፥ |
እርሱም፣ “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፤ አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፤ ጽና” አለኝ። እየተናገረኝም ሳለ፣ በረታሁና፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አበርትተኸኛልና ተናገር” አልሁት።
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።
ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተመራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር በረታ።