መዝሙር 125:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣ እግዚአብሔር ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ያስወግዳቸዋል። በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ክፉ አድራጊዎችን በምትቀጣበት ጊዜ የአንተን መንገድ የተዉትን ከሐዲዎችንም አብረህ ቅጣቸው። ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይሰበስባሉ። |
ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።
ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣ እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከእነርሱም ጋራ የሰላም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ቃል ኪዳኑም የዘላለም ይሆናል። አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ፤ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ።
በዚያ ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፣ በምድርም ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋራ፣ ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ ሁሉም ያለ ሥጋት እንዲኖሩ፣ ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን፣ ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው።
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ካወቃቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመታዘዝ በደሙ ለተረጩትና በመንፈስ አማካይነት ለተቀደሱት፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።