መዝሙር 118:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተገፍትሬ ልወድቅ ተንገደገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን ረዳኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገፈተሩኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፥ ጌታ ግን አገዘኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርቱ ጥቃት ደርሶብኝ፥ ለመውደቅ ተቃርቤ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ረዳኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአፍህን ፍርድ ሁሉ በከንፈሬ ነገርሁ። |
ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ፣ እርሱ ራሱ ደግሞ ያንኑ ተካፈለ፤ ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው፤
ዳዊት ግን፣ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በነፍስህ እምላለሁ በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ።
ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፣ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፣ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።