እርሱ ግን በካም ምድር ድንቅ ሥራ፣ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ።
በዚያ ሳሉ ያደረገላቸውን አስደናቂ ነገሮችና፥ በቀይ ባሕርም ያደረገላቸውን አስገራሚ ነገሮች ዘነጉ።
የምስጋና መሥዋዕትም ይሠዉለት፥ በደስታም ሥራውን ይንገሩ።
እስራኤል ወደ ግብጽ ገባ፤ ያዕቆብ በካም ምድር መጻተኛ ሆነ።
የዐፍላ ጕልበታቸው መጀመሪያ የሆኑትን በካም ድንኳን፣ በኵሮቻቸውንም ሁሉ በግብጽ ምድር ፈጀ።
አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤ በኀያላን ውሆች፣ እንደ ብረት ሰጠሙ።