የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤ የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ።
የዱር አራዊትን ሁሉ ያጠጣሉ፥ የበረሃ አህያዎችም ጥማቸውን ያረካሉ።
በዚህ ዐይነት የዱር አውሬዎች የሚጠጡት ውሃ ያገኛሉ፤ የሜዳ አህዮችም ጠጥተው ጥማቸውን ያረካሉ።
ለእስራኤልም ለዘለዓለም የሚኖር ኪዳኑን፤ እንዲህም አለው፥ “ለአንተ የከነዓንን ምድር፥ የርስታችሁ ገመድ ትሆናችሁ ዘንድ እሰጣለሁ፤”
ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች።
አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።