ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከርሷም ጋራ ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
ምሳሌ 9:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የበሉት ምግብ ይጥማል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የስርቆት ውኃ ይጣፍጣል፥ የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰርቀው የሚጠጡት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የሚበሉትም እንጀራ ያስደስታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የተሸሸገ እንጀራን አሰማምረህ ዳስስ። ጣፋጭ የስርቆት ውኃንም ጠጣ፥” |
ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከርሷም ጋራ ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።