ምሳሌ 8:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያጣኝ ሁሉ ግን ራሱ ይጐዳል፤ የሚጠሉኝም ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፥ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ያጣ ራሱን ይጐዳል፤ እኔን የሚጠላም ሞትን ይወዳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ። |
እንዲህ በላቸው፤ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዳቸው ተመልሰው በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ በክፉዎች ሞት ደስ አልሰኝም። ተመለሱ! ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለምን ትሞታላችሁ?’
ጳውሎስና በርናባስም በድፍረት እንዲህ አሏቸው፤ “የእግዚአብሔር ቃል በመጀመሪያ ለእናንተ መነገር አለበት፤ እናንተ ግን ናቃችሁት፤ በዚህም የዘላለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ላይ ስለ ፈረዳችሁ፣ እኛም ወደ አሕዛብ ዞር ለማለት እንገደዳለን።
ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ተራ ነገር የቈጠረ፣ የጸጋንም መንፈስ ያክፋፋ እንደ ምን ያለ የባሰ ቅጣት ይገባው ይመስላችኋል?
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን።