ምሳሌ 8:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማያትን በዘረጋ ጊዜ፣ በውቅያኖስ ላይ የአድማስ ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ በቀላያት ፊት ክበብን በደነገገ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሰማይን በዘረጋ ጊዜ፥ ጠፈርንም ከውቅያኖሶች በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፥ እኔ እዚያ አብሬው ነበርኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ ዙፋኑን በነፋሳት ላይ ባጸና ጊዜ፥ |
እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።
ሁሉ ነገር በርሱ ተፈጥሯል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በርሱና ለርሱ ተፈጥሯል።