ምድርን ወይም ሜዳዎቿን፣ ወይም ምንም ዐይነት የዓለም ትቢያን ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ።
ምድሪቱንና ሜዳውን ገና ሳይፈጥር፥ የመጀመሪያውንም የዓለም አፈር።
እግዚአብሔር ምድርን ሁሉ ከመፍጠሩ በፊት፥ ወይም የመጀመሪያው ዐፈር እንኳ ከመፈጠሩ በፊት ተወለድኩ።
እግዚአብሔር ከሰማይ በታች የሚታደርባቸውን ሀገሮችንና ዳርቻዎችን ሳይፈጥር።
ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ ከኰረብቶችም በፊት ተወለድሁ፤
ሰማያትን በዘረጋ ጊዜ፣ በውቅያኖስ ላይ የአድማስ ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፤