ምሳሌ 8:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከውቅያኖሶች በፊት፣ የውሃ ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ ተወለድሁ፥ የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የውሃ ምንጮች ከመፍለቃቸው፥ ውቅያኖሶችም ከመገኘታቸው በፊት ተወለድኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀላያትን ሳይፈጥር፥ የውኃ ምንጮችም ሳይፈልቁ፥ |
በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።
እግዚአብሔር፣ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤” ወይስ ደግሞ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?
እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ።