ምሳሌ 8:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክርና ትክክለኛ ጥበብ የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል አለኝ፤ ብርታት አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፥ ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምክርና መልካም ጥበብ ከእኔ ይገኛሉ፤ ማስተዋልና ብርታትም የእኔ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምክርና ሥልጣን የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል የእኔ ነው፥ ብርታትም የእኔ ነው። |
ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር?
ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
ዕቅድህ ታላቅ፣ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ዐይኖችህ የሰው ልጆችን መንገዶች ሁሉ ያያሉ፤ ለእያንዳንዱም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ።