ምሳሌ 7:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቷ ወደ ሲኦል የሚወስድ፣ ወደ ሞት ማደሪያም የሚያወርድ ጐዳና ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው፥ ወደ ሞት ማደርያዎች የሚወርድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርስዋ ቤት የሚወስደው መንገድ ወደ ሞትና ወደ መቃብር የሚያወርድ ጐዳና ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቷ ወደ ሞት ጓዳ የሚያወርድ የሲኦል መንገድ ነው። |
ልቧ ወጥመድና አሽክላ፣ እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣ ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤ አምላክን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ አመንዝሮች፣ ወንደቃዎች፣ ግብረ ሰዶማውያን፣