ምሳሌ 4:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግርህን ጐዳና አስተካክል፤ የጸናውን መንገድ ብቻ ያዝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮችህ በቀና መንገድ ላይ ይራመዱ። መንገድህም ሁሉ ይቃናልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥ መንገዶችህንም አቅና። |
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋራ በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ነቀፋ የሌለባችሁና ቅዱሳን ሆናችሁ እንድትገኙ ልባችሁን ያጽና።
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።