ምሳሌ 4:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥመትን ከአፍህ አስወግድ፤ ብልሹ ንግግርም ከከንፈሮችህ ይራቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፥ አሳሳች ቃሎችን ከአንተ አርቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ንግግር ከአፍህ አይውጣ፤ ሐሰትንና ማታለልን ከአንተ አርቃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥ ሐሰተኞች ከንፈሮችንም ከአንተ አስወግድ። |
ስለዚህ ርኩሰትንና ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ክፋትን አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን፣ በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።