ምሳሌ 3:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን በእጅህ እያለ፣ ጎረቤትህን፣ “ቈይተህ ተመለስ፤ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ፥ ወዳጅህን፦ “ሂድና ተመለስ፥ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቸገረ ጐረቤትህን ዛሬውኑ መርዳት ሲቻልህ “እሺ ነገ” እያልክ አታመላልሰው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ፥ ወዳጅህን፦ “ሂድና ተመለስ፤ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው፥ ነገ የምትወልደውን አታውቅምና። |
እንግዲህ በዚህ ነገር በእናንተ ላይ ያለን ትምክሕት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር፣ አስቀድሞ ስለ እናንተ እንደ ተናገርሁት ተዘጋጅታችሁ እንድትገኙ ወንድሞችን ልኬአለሁ።