ምሳሌ 24:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራ ጊዜ ፈራ ተባ ካልህ፣ ዐቅምህ ምንኛ ደካማ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራ ቀን ብትዝል፥ በእርግጥም ጉልበትህ ትንሽ ነው ማለት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከራ በሚደርስብህ ጊዜ መጽናት የማትችል ከሆንክ ምንም ብርታት የለህም ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከራ ቀንና በክፉ ቀን እስኪያልቅ ድረስ ያረክሰዋል። |
ወሬ በምድሪቱ ሲሰማ፣ ተስፋ አትቍረጡ፤ አትፍሩም፤ ገዥ በገዥ ላይ ስለ መነሣቱ፣ ዐመፅም በምድሪቱ ስለ መኖሩ፣ አንድ ወሬ ዘንድሮ፣ ሌላውም ለከርሞ ይመጣል፤
የሰይጣን ዙፋን ባለበት እንደምትኖር ዐውቃለሁ፤ ሆኖም ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል። ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ ከተማ የተገደለው ታማኙ ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።
ዳዊት ግን በልቡ፣ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፣ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ ዐሰበ።