ምሳሌ 23:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሥሥታምን ምግብ አትብላ፤ ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንፉግን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የስስታምን እንጀራ አትብላ፤ የሚያቀርብልህም ጥሩ ምግብ አያስጐምጅህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከስስታም ሰው ጋር አትመገብ፥ ምግቡንም አትመኝ፤ |
“ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል” የሚል ምናምንቴ ሐሳብ ዐድሮብህ፣ በድኻ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፣ እርሱም በአንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!
በመካከልህ ተለሳልሳና ተቀማጥላ የምትኖር፣ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ፣ እግሯን ዐፈር ነክቶት የማያውቅ ሴት፣ የምትወድደውን ባሏን፣ የገዛ ወንድ ወይም ሴት ልጆቿን ትንቃለች።