ምሳሌ 23:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከገዥ ጋራ ለመብላት በምትቀመጥበት ጊዜ፣ በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባለ ሥልጣን ጋር ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ በፊትህ ያለውን በደኅና አስተውል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከባለ ሥልጣን ጋር ለመመገብ በአንድ ገበታ ላይ ብትቀርብ ማንነቱን አትዘንጋ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመኳንንት ማዕድ ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ ያቀረቡልህን ፈጽመህ ዕወቅ፤ |
እነዚህ ሰዎች በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ያለ አንዳች ኀፍረት ከእናንተ ጋራ ቀርበው የሚበሉ ነውረኞች ናቸው፤ ደግሞም ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው፤ እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው ከሥራቸው ተነቅለው ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።