ምሳሌ 22:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢባንን ቃል ልብ ብለህ ስማ፤ ልብህም ወደ ትምህርቴ ያዘንብል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጆሮህን አዘንብለህ የጠቢባንን ቃላት ስማ፥ ልብህንም ወደ እውቀቴ አድርግ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠቢባን ሰዎች የተናገሩትን ሳስተምርህ አድምጥ፤ ከእነርሱ የምታገኘውን ትምህርት አጥና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ የእኔንም ቃል ስማ፥ መልካምንም ታውቅ ዘንድ ልብህን አቅርብ። |
የጠቢባን ቃላት እንደ ሹል የከብት መንጃ ናቸው፤ የተሰበሰቡ አባባሎቹም እጅግ ተቀብቅበው እንደ ገቡ ችንካሮች ሲሆኑ፣ ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው።
ጆሯችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ። ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
እርሱ እየተናገረ ሳለ፣ ብሩህ ደመና ሸፈናቸው፤ ከደመናውም ውስጥ፣ “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ ተሰማ።