ምሳሌ 22:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልብ ንጽሕናን ለሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልብን ንጽሕናን የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልብ ንጽሕናንና መልካም ንግግርን የሚወድ ሰው በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የልብን የውሀት ይወድዳል። ንጹሓንም ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተመረጡ ናቸው። ንጉሥ በከንፈሩ ይገዛል። |
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር።