ምሳሌ 21:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ግን ለመጉደል ይቸኩላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥንቃቄ በወጣ ዕቅድ የሚሠራ ሥራ ትርፍ ያስገኛል፤ ያለ ዕቅድ በችኰላ የሚሠራ ሥራ ግን ያደኸያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የትጉህ ዐሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል። |
ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።