ምሳሌ 21:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ያርፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማስተዋል መንገድ የሚርቀውን ሰው ሞት ይጠብቀዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል። |
እንደ በጎች ለሲኦል የተዳረጉ ናቸው፤ ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤ ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤ አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣ በሲኦል ይፈራርሳል።
“ጻድቅ ሰው ግን ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት ቢሠራ፣ ኀጢአተኛው የሚያደርገውንም አስጸያፊ ነገር ቢፈጽም፤ ይህ ሰው በውኑ በሕይወት ይኖራልን? ከሠራው ጽድቅ አንዱም አይታሰብለትም፤ ታማኝነቱን በማጕደሉና ከፈጸመው ኀጢአት የተነሣ ይሞታል።
ከእኛ መካከል ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋራ ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ ይታወቅ ዘንድ ከእኛ ተለዩ።
እነዚህ ሰዎች በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ያለ አንዳች ኀፍረት ከእናንተ ጋራ ቀርበው የሚበሉ ነውረኞች ናቸው፤ ደግሞም ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው፤ እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው ከሥራቸው ተነቅለው ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።